በ2018 የትምህርት ዘመን ማንኛውም የአዲስ አበባ ተማሪ የፋይዳ መታወቂያ ከሌለው ምዝግገባ ማድረግ አይችልም ተባለ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከወሳኝ ኩነት ጋር በመሆን ከ5 አመት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን መመዝገብ ተጀምራል።
በአዲስ አበባ ከተማ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የሚሆኑ ተማሪዎች መኖራቸውን ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጸህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎችን መመዝገብ እንደተጀመረም አስታውቀዋል።
በዚህም በአንድ ወር ውስጥ ከ450ሺ በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህ የተማሪዎች ምዝገባ በግልም ሆነ በመንግስት እንዲሁም የትኛውም የኮሚኒቲ እና ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ መመዝገብ አለባቸው።
የአዲስ አበባ ተማሪዎችን በኢ ስኩል ሲስተም ለመመዝገብ ከአሁን በፊት መጀመሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ መግለፁ የሚታወስ ሲሆን ይህንን አሰራር ለማገዝ የፋይዳ መታወቂያ የአንድን ተማሪ ሙሉ መረጃ የሚያሳይ በመሆኑ ቅድሚ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ኢንጂነር ወንድሙ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።
አስካሁን ከ5 ሚሊየን በላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተነግሯል። በቀጣይም ማንኛውም የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶች ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ አስገዳጅ ይሆናል።
@Yenetube